Fana: At a Speed of Life!

አል ሲሲ ለሦስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብጹ ፕሬዚዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ በመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ ሊወዳደሩ መሆኑ ተሰማ፡፡

ግብጽ ከፈረንጆቹ ታሕሳስ 10 እስከ 12 ቀን ድረስ ምርጫ ታካሂዳለች፡፡

አል ሲሲ የሀገሪቱ ፖለቲከኞች በተገኙበት ብሄራዊ ጉባዔ ላይ ነው ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫው እጩነታቸውን ያስታወቁት።

አል ሲሲ በንግግራቸው ፥ በመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ወስኛለሁ ብለዋል።

አል ሲ ሲ በምርጫው እሳተፋለሁ ቢሉም በሃገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም እና የዋጋ ግሽበት መናር አሸናፊነታቸው ላይ ጥርጣሬ አሳድሯል መባሉን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አመላክቷል፡፡

የቀድሞው የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር የአሁኑ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ግብጽን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

እጩዎች ከሕዳር 9 እስከ 29 የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉ ሲሆን ፥ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የግብፅ ስደተኞች ደግሞ ከታህሳስ 1 እስከ 3 ድምጽ እንደሚሰጡም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.