ኢትዮጵያና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 22 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ፍራንሷ ኤድሊ ፎሎት የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል፡፡
ፍራንሷ ኤድሊ ፎሎት÷በፈረንጆቹ 2010 የተፈረመውን የሀገራቱን የአየር ትራንስፖርት ሥምምነት በጥናት ወቅቱን ባማከሉ ዓለም ዓቀፍ አሰራሮች በማደስ ትብብራቸውን ዳግመኛ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2015 ከአዲስ አበባ ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከተማ ባንጊ በረራ ያካሂድ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡፡
ይሁን እንጂ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ አየር መንገዱ ወደ ባንጊ የሚያደርገው በረራ ተቋርጦ መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ ዓመት ኅዳር ወር አጋማሽ ጀምሮም በረራው እንደሚቀጥል መገለጹን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን መረጃ ያመላክታል፡፡