Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ያዘጋጀውን የኮቪድ19 ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ያዘጋጀውን የኮቪድ19 ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል ጎበኙ።

ዶክተር ሊያ በጉብኝታቸው ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ ቫይረሱን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች ዞኖች የተዘጋጁ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን እየደገፈ መሆኑ የሚበረታታ ነው ሲሉ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

አያይዘውም ወደፊትም የመከላከል ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ማዕከላዊ ጎንደር ዞንና በጎንደር ከተማ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባይገኝም ወደፊት ለሚገጥሙ ችግሮች ግን ሆስፒታሉ 310 አልጋዎች ያሉት የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል አዘጋጅቷል።

እንዲሁም ለለይቶ ማቆያ የሚሆኑ 3 ሺህ ክፍሎችም መዘጋጀታቸው ታውቋል።

በህክምና ማዕከሉ የምርመራና ላቦራቶሪ አገልግሎቶችና አስፈላጊ ግብአቶችም ተዘጋጅተዋል።

በጉብኝቱ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.