Fana: At a Speed of Life!

ከእርድ ጥቅሞች በጥቂቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እርድ የቅመም ዓይነት ሲሆን፥ አብዛኛውን ጊዜ ቀለምንና ጣዕምን ለማምጣት በምግብ ላይ ይጨመራል።

እርድ የጸሐይ ብርሃንና ብክለትን በመከላከል ሴሎችን ከጉዳት በማስወገድ ሰውነትን ሊከላከሉ በሚችሉ ንጥረ-ነገሮች የበለፀገ እንደሆነ ጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በጤና መረጃው ያነሳል።

ከዕፅዋት በተቀመሙ የበለፀጉ ምግቦች እንደ ካንሰር እና የልብ ሕመም ያሉ የሕክምና ሁኔታዎችን ከመከላከል ጋር የተያያዙ እንደሆነ ይነሳል፡፡

እርድ እብጠትን ለመቀነስ፣ ለዓይን ጤንነት፣ የልብና የስትሮክ እንዲሁም የዓይነት 2 የስኳር በሽታ ይከላከላል፣ የአንጓ ብግነት ይከላከላል እንዲሁም በደም ውስጥ ያለውን ኮሌስትሮል እንዳይጨምር ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ጭንቀትን ያስወግዳል፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከተደረገ በኋላ የሚከሰትን የጡንቻ ህመም ለማስወገድ እና ለኩላሊት ጤንነት ፍቱን ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም ከመጠን ያለፈ እርድ መጠቀም ለችግር ሊያጋልጥ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን፥ እንደአብነትም የኩላሊት ጠጠር እንዲከሰት ሊያደርግ ስለሚችል ጥንቃቄ ያድርጉ ብሏል በዘገባው፡፡

በተጨማሪም እርድ ለአንዳንድ ሰዎች አለርጂ ሊሆን ስለሚችል ቀደም ብሎ መጠንቀቅና አለርጂ እንዳልሆነ በማረጋገጥ በአግባቡና በመጠኑ መውሰድ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.