Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የ12 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ12 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።

አምባሳደሮቹም በኢትዮጵያ የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሌሴቶ፣ ሩዋንዳ፣ ባንግላዲሽ፣ ፓኪስታን፣ ፊንላንድ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒካራጓ እና ሉክሰምበርግ አምባሳደሮች ናቸው።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአምባሳደሮቹ ጋር ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ምቹ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

አምባሳደሮቹ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ለተሾሙት የሀገራቱ አምባሳደሮችም መልካም የሥራ ጊዜ መመኘታውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.