ቢዝነስ

የኢትዮ-ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት ተደረገ

By Mikias Ayele

October 04, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው 2024 የኢትዮጵያና ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ከሆኑት ናሻ አልዊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው  በኢትዮጵያ የሞሮኮ ባለሀብቶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማራጮችን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም በመጪው 2024 የኢትዮጵያ ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኮሚሽሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡