የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኮሮና ቫይረስ ምርመራና ህክምና መስጫ ማዕከልን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በወቅቱም የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲን እና የባህር ዳር ከተማ የማገገሚያ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውን ሆስፒታል ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሯ በትናንትናው እለት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ያለውን የኮሮና ምርመራና ሕክምና ማዕከል መጎብኘታቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።