Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለቤት ተከራዮች በግንቦት ወር ክፍያ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ18 ሺህ 153 የቤት ተከራዮች በድጋሚ በግንቦት ወር ክፍያ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ይህንንም ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያበረከተው አስተዋጽፅኦ 130 ሚሊየን ብር መድረሱን አመልክቷል።

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በሽታውን ለመከላከል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስተዋፅኦ ማድረጉን  የገለፀው ኮርፖሬሽኑ፥ ከዚህ በፊት 10 ሚሊየን ብር ለኮቪድ-19 ድጋፍ አሰባሳቢ ብሄራዊ ኮሚቴ ማበርከቱን አስታውሷል።

በተጨማሪም በሚያዚያ ወር በእያንዳንዱ ተከራይ በሚያዚያ ወር ክፍያ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አመለክቷል።

በድጋሚ በግንቦት ወር ክፍያ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ በማድረግ በአጠቃላይ ሊያገኝ የሚችለውን 120 ሚሊየን ብር መቶውን አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ባደረገው የወርሃዊ የክፍያ ቅናሽ 11 ሺህ 860 የመኖሪያና  6 ሺህ 293 የድርጅት ቤቶች በቀጥታ ተጠቃሚ ሆነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.