Fana: At a Speed of Life!

የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለመጨመር፣ ለዕዳ ስረዛና አደረጃጀትን ለመቀየር የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለመጨመር እንዲሁም ለዕዳ ስረዛ እና አደረጃጀትን ለመቀየር የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

የብሔራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ በዛሬው እለት መካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

በዚህም ኮቪድ19 በኢኮኖሚ ላይ ያሳደረውን ጫና እና ለቀጣዩ የበጀት ዓመት የሚደረገውን የበጀት ዝግጅት በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም፣ የዓመቱን ኢኮኖሚያዊ ክንውን ገምገማቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ስብሰባውን አስመልክቱ ባወጡት መልእክትም፦ “ወረርሽኙ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ መቀዛቀዝ ቢያስከትልም፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የበርካታ ዘርፎች አምራችነት እንዳይቋረጥ በሙሉ ዐቅማችን እንሠራለን” ብለዋል።

“የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለመጨመር እንዲሁም ለዕዳ ስረዛ እና አደረጃጀትን ለመቀየር የሚደረጉ ጥረቶችንም አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.