ስፓርት

ፋሲል ከነማ እና ሐዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

By Alemayehu Geremew

October 07, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግማሽ ደርዘን ጎሎች በተቆጠሩበት የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከሐዋሳ ከተማ ሦስት አቻ ተለያይተዋል፡፡

የፋሲል ከነማን ጎሎች ሱራፌል ዳኛቸው (2) እና ጌታነህ ከበደ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማን ደግሞ ታፈሰ ሰሎሞን፣ አሊ ሱሌማን እና በረከት ሳሙኤል አስቆጥረዋል፡፡

የሊጉ መርሐ- ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 1፡00 ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከመቻል ጋር ይጫወታሉ፡፡