ስፓርት

በቱርክ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

By Amele Demsew

October 08, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ አንካራ በተካሄደው የሴቶችና የወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

በወንዶቹ አትሌት ሲሳይ ለማ 1 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡

አትሌት ጪምዴሳ ደበሌ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸናፊ መሆኑንም ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም አትሌት ዘውዲቱ አደራው በሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏም ነው የተሰማው፡፡