Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤልና ሃማስን ግጭት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ እንዳይጨምር ተሰግቷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለትም በእስራኤል እና በጋዛ ያለው ሁኔታ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚመጣውን የነዳጅ ምርት ሊያስተጓጉል ይችላል በሚል ስጋት የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተገልጿል፡፡

የዓለም አቀፉ መለኪያ የሆነው ብሬንት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋን በበርሚል ወደ 87 ነጥብ 68 ዶላር ከፍ ያደረገ ሲሆን፤ በአሜሪካም የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተገልጿል።

ምንም እንኳን እስራኤል እና የፍልስጤም ግዛቶች ነዳጅ አምራች ባይሆኑም የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ከዓለም አቀፍ አቅርቦት አንድ ሶስተኛውን እንደሚይዝ ይገለፃል።

የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መጨመሩን የገለፁት የኃይል አቅርቦት ተንታኙ ሳውል ካቮኒች በአቅራቢያ ባሉ ዋና ዋና የነዳጅ አምራች ወደሆኑ እንደ ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ ያሉ ሀገራት ሊዛመት የሚችል ሰፊ ግጭት ሊፈጠር ይችላል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ግጭቱ ሃማስን ትደግፋለች የሚል ክስ የቀረበባት ኢራንን የሚያካትት ከሆነ እስከ 3 በመቶ የሚሆነው የዓለም የነዳጅ አቅርቦት አደጋ ላይ ነው ሲሉም አክለዋል።

የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ካሮላይን ቤይን የአሜሪካ ማዕቀብ ቢጣልባትም ኢራን በዚህ ዓመት የነዳጅ ምርቷን እንዳሳደገች ተናግረዋል።

ባጠቃላይ የነዳጅ ፍላጎት በዓመቱ የመጨረሻዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ከአቅርቦት በላይ እንደሚሆን በማንሳት ይህም የዋጋ መናሩን ያባብሰዋል ብለው እንደሚጠብቁ ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.