ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ነቦች
👉 የተሰበረውን በመጠገን፣ ልዩነቶቸን በማጥበብ፣ የተጣመመውን በማቃናት እና ስህተቶችን በማረም ሀገርን በማይናወጥ መሰረት ልናፀና ይገባል፣
👉 ቆም ብለን የመጣንበትን መንገድ ገምገመን ያተረፍንበትን በማጠናከር የከሰርንበትን ደግሞ ማስተካከል ይኖርብናል፣
👉 ያደጉ የምንላቸው ሀገራት ዛሬ ላይ የደረሱት ልዩነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ሳይሆን ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት በመቻላቸው ነው፣
👉 ትላንት ለነገ ትምህርት እንጂ እንቅፋት ሊሆን አይገባም፣ የትናንት ታሪክ የአብሮነት መገንቢያ እንጂ የልነት መነሻ እንዳይሆን መስራት አለብን፣
👉 ባለፉት ዓመታት በፈተና እና በተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ተመዘግበዋል፣
👉 ኢኮኖሚያችን አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ነው፣ ከነጠላ ዘርፍ ወደ ባለ ብዙ ዘርፍ አኮኖሚነት ተሸጋግሯል፣ ሀገራዊ የልማት ግቦችም በተያዘላቸው ጊዜ እየተከናወኑ ነው፣
👉 ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏብሔራዊ የዲፕሎማሲ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል፣
👉 ተነጋግረን ባንግባባም ጦርነት አማራጭ ሆኖ መቅረብ የለበትም፣ በጦርነት አንድ አሸናፊ ይኖራል፣ በውይይት ግን ሁሉም አሸናፊ ነው፡፡