Fana: At a Speed of Life!

የኮማንዶና ዓየር ወለድ ዕዝ አዛዥ የሠራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮማንዶና ዓየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በሰሜን ሸዋ ዞን በግዳጅ ላይ የሚገኙትን የሠራዊት አባላት የግዳጅ አፈፃፀም እና ቀጠናውን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም÷ የክፍሉ የሠራዊት አባላት ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሕዝቦች ሰላም በጀግንነት የፈፀሟቸውን ግዳጆች አወድሰዋል፡፡

ለሕዝባችሁ፣ ለሀገራችሁ ሰላምና ደኅንነት ፅንፈኛ ኃይሉን ተጋፍጣችሁ ለፈፀማችሁት ገድል ክብርና ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ አበረታትተዋል፡፡

የክፍሉ አባላት የኢትዮጵያን አንድነት ከነ ሕዝቦቿ ለማስቀጠል በፅናት ቆሞ በመፋለም ለትውልድ የሚሻገር ታላላቅ ድሎች ማስመዝገባቸውንም ነው አዛዡ ያስታወሱት፡፡

የሠራዊቱ አባላት በበኩላቸው÷ የሀገራቸውንና የሕዝባቸውን ክብር ለተቀጣሪ ባንዳዎች አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡

ከአባቶቻችን የተቀበልናትን አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ ለትውልድ ለማስተላለፍ በትጋት እንቆማለን ነው ያሉት፡፡

ከፅንፈኛ ኃይሉ ዲሽቃን ጨምሮ ሌሎች መሳሪያዎችን ማርከናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.