ስፓርት

ኤዲን ሃዛርድ ጫማ ሠቀለ

By ዮሐንስ ደርበው

October 10, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ ተጫዋች ኤዲን ሃዛርድ በ32 ዓመቱ ራሱን ከእግርኳስ ማግለሉን አስታወቀ፡፡

ሃዛርድ÷ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ ባጋጠሙት ተደጋጋሚ ጉዳቶች የመሰለፍ ዕድል ማጣቱ ይታወሳል፡፡

ምንም እንኳን ቀሪ የኮንትራት ጊዜ ቢኖረውም ከማድሪድ ጋር በስምምነት መለያየቱን ነው የገለጸው፡፡

ሃዛርድ በተለይም ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጋር ስኬታማ የሚባል ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን፥ ‘ወርቃማ’ የተባለውና በውጤት ያልታጀበው የቤልጂየም ብሄራዊ ቡድንም አባል ነበር።

ከቼልሲ ጋር ከተለያየ በኋላ በስፔኑ ሃያል ክለብ የታሰበውን ያህል ግልጋሎት ባይሰጥም ከክለቡ ጋር ቻምፒየንስ ሊግ እና የስፔን ላ ሊጋን ጨምሮ ስምንት ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።