Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢኒስቲትዩት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢኒስቲትዩት የስራ ሃላፊዎች ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

ቶኒ ብሌይር ኢኒስቲትዩት በኢንቨስትመንት እቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ ዘርፍ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ መታደጊያ ፋይናንስ ማፈላለግ ላይ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት÷ ኢንስቲትዩቱ ከተቋማቸው ጋር የሚሰራቸው የትብብር ስራዎች ውጤት ያመጡና የእውነተኛ ትብብር ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ትብብሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲዔታ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢንስቲትዩቱ በክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስቴሩ እየሰራ ያለውን ስራ በቴክኒክ እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችና ሌሎች አጋዥ ሰነዶችም በጋራ እየተዘጋጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የፐብሊክ ኢንቨስትመንት አስተዳደርን በተመለከተ በዩናይትድ ኪንግደም የዳበረ ልምድ መኖሩን በመግለጽ ኢንስቲትዩቱ ኩባንያዎችን የማስተሳሰርና ልምድ የሚገኝበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

ኢኒስቲትዩቱ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የጀመራቸውን የትብብር ስራ እንደሚያጠናክር ያረጋገጡት ደግሞ÷ የቶኒ ብሌይር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ማለዳ ብስራት ናቸው፡፡

ለ28ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብርት ለውጥ ጉባዔ እየተደረገ ያለው ዝግጅትም በመድረኩ መቅረቡን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.