የተቋረጠው ትምህርት ሲቀጥል ጫና እንዳይፈጥር የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ግንቦት 9፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ሲቀጥል ጫና እንዳይፈጥር የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዚህም የተቋረጠው የትምህርት ዘመን በምን መልኩ መቀጠል እንዳለበት የሚያጠና ቡድን ተደራጅቶ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የትምህርት ቤቶች መዘጋት ሲሆን ከመጋቢት መጀመሪያ አንስቶም በአገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው ቆይተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ ÷በወረርሽኙ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ እንዲሆኑ በመወሰኑ ተማሪዎች በሬዲዮና ቴሌቪዥን እየተማሩ ይገኛሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።