Fana: At a Speed of Life!

በሐረማያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረማያ ወረዳ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች፡፡

በወረዳው ሸሪፍ ካሊድ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ማሪያ መሐመድ ሙሜ ዛሬ ጠዋት ነው በሐረማያ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን የተገላገለችው፡፡

የተወለዱት ሕጻናት ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ ÷ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሠለሞን ታምራት÷ እናት አራት ልጆቹን በቀዶ ሕክምና እንድትገላገል መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሕጻናቱ ከ1 ነጥብ 4 እስከ 1 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም እንደሚመዝኑ ገልጸው÷ አሁን ላይ እናት እና ሕጻናቱ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.