ስፓርት

ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አስመዘገበ

By Meseret Awoke

October 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በጫላ ተሽታ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 6 በማድረስ ሊጉን በበላይነት መምራት ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1ለ 0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን÷ከድር ኩሉባሊ በራሱ ግብ ላይ ያስቆጠራት ግብ ንግድ ባንክን አሸናፊ ባለቤት አድርጎታል።