በመዲናዋ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈቃድ የወሰዱ አካላት ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈቃድ የወሰዱ አካላት ወደ ጅምር የግንባታ ስራ መግባታቸውን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በባለስልጣኑ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ ዳይሬክተር ከማል ጀማል (ኢ/ር)÷ በ2016 በጀት ዓመት በመዲናዋ በኮንስትራክሽን ዘርፉ 3 ሺህ 110 አካላት የግንባታ ፈቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 900 ያህሉ የግንባታ ማሻሻያ ፈቃድ የወሰዱ መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በኮንስትራክሽን ሕንጻ ግንባታ ዘርፍ ፈቃድ የወሰዱ አካላትም ወደ ጅምር የግንባታ ስራ መግባታቸውን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
ወደ ግንባታ ስራ የገቡ አካላት የግንባታ መስፈርቱን ተከትለው እንዲያከናውኑም የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ