ስፓርት

ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በአቻ ውጤት ተለያዩ

By Melaku Gedif

October 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወልቂጤ ከተማና ሲዳማ ቡና 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማን ግብ በተጨማሪ ደቂቃ ተመስጌን በጅሮንድ ሲያስቆጥር÷የሲዳማ ቡናን ደግሞ በተጨማሪ ደቂቃ ደስታ ደሙ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ አዳማ ከተማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የአዳማ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኤልያስ ለገሰ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡