ስፓርት

የደልሂ ግማሽ ማራቶን በአትሌት አልማዝ አያና አሸናፊነት ተጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

October 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ በተካሄደው 18ኛው የደልሂ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር አትሌት አልማዝ አያና አሸነፈች፡፡

ርቀቱን ለማጠናቀቅም 1 ሰዓት ከ 7 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ፈጅቶባታል።

አትሌቷ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተመልሳ ያስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ2016 የሪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ አትሌት አልማዝ አያና ከ6 ዓመታት በፊትም በደልሂ በተካሄደ ተመሳሳይ የግማሽ ማራቶን ውድድር ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!