ስፓርት

በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት መሠረት በለጠ አሸነፈች

By Feven Bishaw

October 15, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መሰረት በለጠ በአምስተርዳም ማራቶን አሸናፊ ሆናለች።

አትሌት መሰረት ርቀቱን 2 ሰአት ከ18 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ነው አሸናፊ የሆነችው።

አትሌቷ ባለፈው አመት ጥር ወር በኳታር ዶሃ ካሸነፈች በኋላ የዛሬው ሁለተኛ ድሏ መሆኑን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል።