Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን ባለብዙ ዘርፍ የእድገት አላማ ብሎም የተገኙ ድሎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም ከቻይና ጋር የንግድ ግንኙነቶችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ በበኩላቸው ፥ ሁለቱ ሀገራት በማደግ እና በመጎምራት ላይ ያለ ኢኮኖሚ ባለቤቶች እንደመሆናቸው በጋራ የማደጊያ መንገዶችን ሊቀይሱ እንደሚችሉ አውስተዋል።

ከውይይታቸው በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች በተፈረሙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.