ቢዝነስ

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዱባይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዐውደ- ርዕይ እየተሳተፉ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

October 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ሀገር የንግድ ሥራዎችን በሀገር ውስጥ በመሥራት ላይ የተሠማሩ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዱባይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዐውደ- ርዕይ ላይ እየተሳተፉ ነው።

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉና የውጭ ሀገር የንግድ ሥራዎችን በሀገር ውስጥ በማከናወን ላይ የተሠማሩት÷ አፍሪኮም ቴክኖሎጂ፣ ኢ ቴክ ቴክኖሎጂ እና ኤም ኤም ሲ ዋይ ቴክ በዐውደ- ርዕዩ እየተሳተፉ ነው፡፡

መድረኩ ኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራዎችን በሀገር ውስጥ ለመሥራት ያላትን ዐቅም ለማስተዋወቅና ሥራዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡

በውደ- ርዕዩ ላይ ከ6 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እና 1 ሺህ 800 ጀማሪዎች ይሳተፋሉ መባሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ1 ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ዐውደ- ርዕዩን ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!