ኢትዮጵያ ታሪክ ጠገብ ሀገር ናት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ታሪክ ጠገብ ሀገር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ÷ በአፍሪካ በእስያ እና አውሮፓ መካከል መገናኛ በር አድርጎ ያቆያት መልክአ ምድራዊ አድራሻ ባለቤት መሆኗንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡
የቤልት እና ሮድ ኢኒሼቲቭ ይህንን እድል አገልግሎት ላይ ለማዋል ብሎም በቀጠናችን ያለንን የንግድ ኢንቨስትመንት እና የቁርኝት ማእከልነት ለማጠናከር ልዩ አጋጣሚ ይሰጠናል ብለዋል::