ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት መርሐ ግብሮች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

By Alemayehu Geremew

October 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ አዳማ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ እንዲሁም ኢትጵያ ቡና ከባህር ዳር ከተማ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡

ለአዳማ ከተማ አብዲሳ ጀማል እና ዮሴፍ ታረቀኝ እንዲሁም ለሀምበሪቾ ዱራሜ በፍቃዱ አስረሳኸኝ እና ዳግም በፍቃዱ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

በውጤቱ መሰረት አዳማ ነጥቡን ወደ 5 ከፍ በማድረግ የነበረበትን 6ኛ ደረጃ ሲያስጠብቅ÷ ከሦስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት የቻለው ሀምበሪቾ ዱራሜ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

እንዲሁም ጫላ ተሽታ እና ብሩክ በየነ ለኢትዮጵያ ቡና÷ ቸርነት ጉግሳ እና ፍፁም ጥላሁን ደግሞ ለባህዳር ከተማ ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል፡፡

ውጤቱን ተክትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ7 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባህርዳር ከተማ በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡