Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ታንዛኒያ ወዳጅነት ቡድን ከታንዛኒያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮ-ታንዛኒያ ወዳጅት ቡድን በኢትዮጵያ ከታንዛኒያ አምባሳደር ኢኖሰነት ኢ ሺዮ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዷል፡፡

በኢትዮጵያ የታንዛኒያው አምባሳደር ኢኖሰነት ኢ ሺዮ ÷ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በግብርና በኢንቨስትመንትና በሌሎችም መስኮች የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግንኙነቱ በሌሎች መስኮችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው አምባሳደሩ የገለጹት፡፡

የወዳጅነት ቡድኑ ሰብሳቢ አምባሳደር ሺመብራት መርሻ (ዶ/ር) ÷ ሁለቱ ሀገራት አብረው የሚሰሩባቸው ዘርፎች በርካታ እንደሆኑ በመግለጽ ያሉትን ግንኙነቶች አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከርና በፓርላማ አሰራርና አተገባበር ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ያለመ መሆኑን ነው የምክር ቤቱ መረጃ የሚያመላክተው፡፡

የኢትዮጵያና ታንዛኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው በ1961 መሆኑ እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተጠናከረ እንደመጣም በውይይቱ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል የመጀመሪያ የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመው በ1965 እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን÷እስካሁን ድረስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከ19 በላይ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል ነው ያሉት፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.