Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በትናትናው ዕለት የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዋና ፀሃፊው ሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነትን ፣ ሁሉንም አሸናፊ ፣ አለም አቀፍ ህጎችን መርሁ ያደረገውን የ2015ቱን የመርሆች ስምምነት ትኩረት እንዲያደርጉበት አሳስበዋል።
በቀጣይም እነዚህ መርሆችን መሰረት ያደረገ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ፍላጎታቸው መሆኑን ዋና ፀሃፊው አስታውቀዋል።

እንዲሁም ሀገራቱ በግድቡ ዙሪያ ስምምነት ላይ እየታየ ያለው መሻሻል አድንቀዋል።

የአውሮፓ ህብረትም የአባይ ወንዝ እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ላላቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እውቅና እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 73 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ ከፊታችን ሐምሌ ወር ጀምሮ ውሃ መያዝ እንደሚጀምር መገለፁም ይታወሳል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.