Image processed by CodeCarvings Piczard ### FREE Community Edition ### on 2020-02-12 05:27:26Z | http://piczard.com | http://codecarvings.com

የሀገር ውስጥ ዜና

ተመድ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ ጠየቀ

By Tibebu Kebede

May 20, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በትናትናው ዕለት የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ፀሃፊው ሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነትን ፣ ሁሉንም አሸናፊ ፣ አለም አቀፍ ህጎችን መርሁ ያደረገውን የ2015ቱን የመርሆች ስምምነት ትኩረት እንዲያደርጉበት አሳስበዋል። በቀጣይም እነዚህ መርሆችን መሰረት ያደረገ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ፍላጎታቸው መሆኑን ዋና ፀሃፊው አስታውቀዋል።