ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጣና ሞገዶቹ ድል ቀንቷቸዋል

By ዮሐንስ ደርበው

October 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአራተኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

12፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ጨዋታ÷ ሀብታሙ ታደሰ የባሕርዳር ከተማን ሦስት ጎሎች በማስቆጠር ሃትሪክ ሠርቷል፡፡

ሃትሪኩም እስካሁን ባለው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር የመጀመሪያው በመሆን ተመዝግቧል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 7 በማድረስ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡

በአንጻሩ ወልቂጤ ከተማ ሁለት ነጥቦችን በመያዝ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

9፡00 ላይ በተከናወነ የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሐዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ያለምንም ግብ ተለያይተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!