ስፓርት

የአራተኛ ሳምንት የዛሬ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

By Tamrat Bishaw

October 27, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

9 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሀምበርቾ ከሀድያ ሆሳዕና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ምሽት 12 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ተገናኝተዋል።

ጨዋታውን አዳማ ከተማ 2 ለ 0 መምራት ቢችልም ከዕረፍት መልስ በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች በአቻ ውጤት አጠናቋል።

ሀይደር ሸረፋ በፍጹም ቅጣት ምት እንዲሁም ዊልያም ሰለሞን በጨዋታ ለአዳማ ከተማ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ተገኑ ተሾመ እና ሞሰስ ኦዶ የአቻነት ጎሎቹን አስቆጥረው ፈረሰኞቹ ከጨዋታው አንድ ነጥብ እንዲያገኙ አስችለዋል።