በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የተገዙ መኪናዎች ለክልሎች ተበረከቱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ መኪናዎች እና ሌሎች ቁሶችን ለክልሎች አስረክቧል፡፡
በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር እና የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡትን ምርጥ ተሞክሮዎች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና የግብርና ልማት ተግባራትን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን የሚረዱ ናቸው ተብሏል፡፡
ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው መኪናዎችና ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ሌሎች የአቅም ግንባታ ድጋፎች ለክልሎች፣ ለወረዳዎችና ለመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል መበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹና የስነ-ምግብ ምርምር ላቦራቶሪዎች በየወረዳዎቹና ተቋማቱ የታቀዱትን ተግባራት በወቅቱ በማከናወን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡