Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በሣይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያውን የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔዋን ልታካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሣይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔዋን ልታካሂድ መሆኗን አስታወቀች።

የሀገሪቱ መንግስት ምክር ቤት መረጃ ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ ነው ጉባዔው በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቾንግቺንግ ማዘጋጃ ቤት በፈረንጆቹ ሕዳር 6 እና 7 እንደሚካሄድ የገለጸው።

ጉባዔው በሣይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ ፈጠራና ልማት፣ በሣይንሳዊ ጥናትና ምርምር ለውጥ፣ በወደፊት ህክምና፣ ሣይንሳዊ ምርምር ለማድረግ እንቅስቃሴ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግና ትልቅ መረጃ ላይ በመንግሥታት መካከልና በህዝብ ለህዝብ የሚደረግ ትብብርና ሽግግር ላይ ያተኩራል ተብሏል።

በኮንፈረንሱ ላይ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ከ70 በላይ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግብዣ እንደተደረገላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ከእነዚህም መካከል የኖቤል ተሸላሚዎች፣ የምርምር ተቋማት፣ የተለያዩ ኢንርፕራይዞች፣ ምሁራን፣ ባለሙያዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች እንደሚገኙበት የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡

ቻይና ከ80 በላይ የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ አጋሮች ጋር የመንግስት ለመንግስት የሣይንስና ቴክኖሎጂ የትብብር ስምምነቶችን መፈራረሟን የሣይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ሚኒስትር ዣንግ ጓንጁን ገልጸዋል።

ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም፥ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ የሣይንሳዊና ቴክኖሎጂ ሽግግርና ትብብርን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የፈጠራ ስነ-ምህዳርን በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሦስተኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በንግግራቸውም የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ትልቁ ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም እንደመሆኑ የካፒታል ልማትን፣ ቴክኖሎጂንና ልምድን በማምጣት ዘላቂ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው ብለዋል።

#Ethiopia #Cihna #BRI

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.