Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ- ልማቶች ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ-ልማቶች ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ፡፡

በመተከል ዞን በከፍተኛ አመራሮች ስምሪት አማካኝነት የተከናወኑ የልማትና የጸጥታ ሥራዎች ግምገማ በግልገል በለስ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ጌታሁን አብዲሳ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ በዞኑ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ- ልማቶችና ተቋማት በሙሉ ዐቅም ወደ ሥራ ለማስገባት ሕዝብን ባሳተፈ ሁኔታ እየተሠራ ነው።

በቀጣናው በከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላም በማስቀጠል የሕብረተሰቡን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ማለታቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዞኑ አበረታች የሰላምና የልማት እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁመው÷ አርሶ አደሩ በሙሉ ዐቅሙ ወደ መደበኛ የግብርና ሥራው እንዲገባ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሁለት ሣምንታት የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም እና ክፍተቶችን በመለየት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.