Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጁባ ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ከሰዓት ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብተዋል።

አቶ ደመቀ ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የዱቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀምስ ሞርጋን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በጁባ በሚኖራቸው ቆይታ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተውእንደሚወያዩ  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተላከ መልዕክትም ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ይሰጣሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.