ስፓርት

10ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

By Feven Bishaw

November 05, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ በሴቶች ፍቅርተ ወረታ ከመቻል ስታሸንፍ፣ ጋዲሴ ሙሉ ከኦሮሚያ ፖሊስ እና የኔነሽ ጥላሁን ከኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

በወንዶች አንዱአለም በላይ ከፌደራል ፖሊስ ውድድሩን አንደኛ በመሆን አጠናቋል።

አትሌት ሰቦቃ ንጉሴ ከኦሮሚያ ክልል እና ክብሮም ደስታ ከኢትዮጵያንግድ ባንክ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው መጨረሳቸውን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።