ስፓርት

በሹዙ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By Meseret Awoke

November 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻይና ሹዙ በተካሄደ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶች ምድብ አትሌት መልካ ደርቤ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ደራርቱ ሃይሉ በሴቶች ምድብ ርቀቱን 2 ሰዓት 27ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፋለች፡፡

አትሌቷ ከዚህ በፊት በቦታው ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ማሻሻል መቻሏንም ፒፕልስ ዴይሊ ኦንላይን ዘግቧል፡፡

በሹዙ 2023 የማራቶን ውድድር በአጠቃላይ ከ30 ሺህ በላይ አትሌቶች ተሳታፊ እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia #China #Marathon

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!