በአዲስ አበባ ተሰብስበው ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው እስከ 20 ሺህ ብር ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው በመሰባሰብ ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 20 ሺህ ብር እና በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የየክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተላለፉት 36 ግለሰቦች ላይ በአቃቤ ህግ ጋር በኩል ክስ እንዲመሰረትባቸው መደረጉን አስታውቀዋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት 21 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እና 20 ሺህ ብሩን መክፈል ያልቻሉ 15ቱ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ15 ቀን እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው የኮሮና ቫይረስ የዜጎችን ህይወትና ጤንነት አደጋ ላይ ሳይጥል ስርጭቱን ለመግታት እንደሆነ ያስታወሱት ሃላፊው፥ ማንኛውም ሰው ራሱን በመጠበቅ እና ለሌሎች በማሰብ ደንብና መመሪያዎችን ማክበር እንዳለበት አሳስበዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።