ቴክ

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን 2 የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አወጣ

By Tibebu Kebede

May 21, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በዛሬው እለት ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አውጥቷል።

ባለሥልጣኑ የፈቃድ አሠጣጥ ሂደቱን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ በተሠጠው ሥልጣን መሠረት እየመራ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለግሉ ዘርፍ የመክፈት ሂደት ዋናው አካል መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንክኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።