ስፓርት

የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆነ

By Mikias Ayele

November 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ሊግ እና የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የክለቦች ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

በዚህ ድልድል በምድብ ሀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀምበሪቾ ዱራሜ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወላይታ ድቻ ከደሴ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከሃላባ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ፣ ነገሌ አርሲ ከስልጤ ወራቤ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከድሬዳዋ ይገናኛሉ፡፡

በተጨማሪም በምድብ ለ ባህርዳር ከተማ ከሸገር ከተማ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከቤንቺ ማጂ ቡና፣ መቻል ከወልቂጤ ከተማ፣ ደብረብርሃን ከተማ ከጋሞ ጨንቻ፣ ፋሲል ከነማ ከነቀምቴ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ከኢትዮ ኤልክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከወልድያ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ከፕሪሚየርሊግ እና ከፍተኛ ሊግ በተወጣጡ 32 ክለቦች መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ ከህዳር 15 እስከ 17 ይደረጋል መባሉን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ 1ኛ ዙር ቀደም ሲል ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን ወደ ቀጣይ ዙር የተቀላቀሉ 16 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች መለየታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አወዳዳሪነት ዘንድሮ የተጀመረ ሲሆን፥ ውድድሩ የሚካሄድበት ቦታ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።