Fana: At a Speed of Life!

299 ሺህ 990 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2ኛው ዙር ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ የገዛው 299 ሺህ 990 ነጥብ 3 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን አስታወቀ።

ከ10 ቀናት በፊት 514 ሺህ 200 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷ ይታወሳል።

እስከአሁን ከውጭ የተጓጓዘው አጠቃላይ የማዳበሪያ መጠን 814 ሺህ 190 ነጥብ 3 ኩንታል እንደሆነም ነው ኮርፖሬሽኑ የገለጸው፡፡

ከዚህ መጠን ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ 434 ሺህ 747 ኩንታል ዩሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የግብርና ሚኒስቴር በየዓመቱ እያጠና በሚያቀርበው የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሰረት ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት 2008 ዓ.ም ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጨረታ እያወጣ የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.