Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ የእጩዎች ጥቆማ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና አባላቶቹ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷ ግልፅና አወዳዳሪ በሆነ አካሄድ እጩዎችን ለማቅረብ ይቻል ዘንድ የእጩዎች መጠቆሚያ ቅፅ (መስፈርት) ለመላው ሕዝብ፣ ለፖለቲካ ድርጅቶች እና ሲቪል ማህበረሰብ መቅረቡን አንስተዋል፡፡

ኮሚቴው ጠቋሚዎች በጥቆማ ሒደት በአንክሮ ሊያስተውሏቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ያሟላ ቅፅ፣ ጥቆማ አቅራቢዎች የሚከተሉትን የጥቆማ ማቅረቢያ መንገዶች እና ጥቆማ የሚቀርብበት የጊዜ ገደብም ይፋ ተደርጓል፡፡

ኮሚቴው ለመላው ህዝብ፣ ለፖለቲካ ድርጅቶችና ለሲቪል ማህበረሰብ እጩዎችን እንዲቀጠቁም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጥቆማውንም ከሕዳር 3 እስከ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚከተሉት አማራጮች ማቅረብ እንደሚቻል ኮሚቴው አስታውቃል፡፡

በኢሜል፡ erc@hopr.gov.et

ዋትስአፕ፡ +251987141100

ቴሌግራም፡ +251987141100

ፖስታ ሳጥን ቁጥር ፡ 80001

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥቅምት 26 ቀን ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ መሰየማቸው ይታወሳል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.