Fana: At a Speed of Life!

የኩላሊት ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኩላሊት ሕመም በዓለማችን እጅግ በአስፈሪ ደረጃ ተስፋፍቶ ያለና የሚታከም ሕመም ነው፡፡

የኩላሊት ሕመም በአዋቂ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች ውስጥ ከ5 በመቶ በላይ የኩላሊት ጉዳት እንዳለባቸው ይነገራል፡፡

በዚህም በየጊዜው የኩላሊት ምርመራ ማድረግ፣ በተለይም ደግሞ የስኳር ታማሚዎች፣ ከፍተኛ ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች፣ ከልክ በላይ ወፍራም ሰዎች፣ በቤተሰባቸው የኩላሊት፣ የስኳር፣ የከፍተኛ የደም ግፊት ሕመም ያለባቸው ሰዎች ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ለመሆኑ የኩላሊት ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ዋና ዋናዎቹ የመከላከያ መንገዶች የተለያዩ ሲሆኑ÷ እነዚህም የኩላሊትና ተያያዥነት ያለው የልብና የደም ስር ህመሞችን በመከላከል በኩል ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ ነው፡፡

የደም ግፊትን ማስተካከል፡- የተስተካከለ የደም ግፊት የኩላሊት ድክመትን ይከላከላል/ያዘገያል።

የሽንት ፕሮቲንን መቀነስ (የደም ግፊትንና የሽንት ፕሮቲንን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን በመጠቀም)፣ በምግብ ላይ ጨው መቀነስ፣ ስኳርንና ቅባትን (ኮሊስትሮል) ማስተካከል፣ ሲጋራ አለማጨስ፣ ስፖርት መስራት እና የሰውነት ክብደትን ማስተካከል ይገባል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.