የግንባታ ሥራዎችን ከአንድ ማዕከል ሆኖ ክትትል ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን ከአንድ ማዕከል ሆኖ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ የሚያስችለውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የለውጥ ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የሚታዩ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ገልጸዋል።
ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው በጀት በማጠናቀቅ በኩል ተወዳዳሪ መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡
ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከ55 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 67 ፕሮጀክቶችን በላቀ ብቃት እየገነባ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የዲጂታል ሥርዓቱ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ በሚፈለገው ጥራትና ፍጥነት እንዲከናወኑ ለማስቻል የላቀ አበርክቶ የሚኖረው መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡