Fana: At a Speed of Life!

የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸንኮራ አገዳ ካርቦሃይድሬት፣ ካሎሪ፣ ፕሮቲን እና ሌሎች ጠቃሚ ይዘቶች ያሉት እና በስኳር ይዘቱ ከፍተኛ የሆነ የተክል ዓይነት ነው፡፡

የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የጤና በረከቶች ምንድን ናቸው?

ኃይልን ያጎናጽፋል፦ እራስዎን ለማነቃቃት እና የሰውነት ፈሳሽ እጥረት እንዳይኖርዎ ለማድረግ መፍትሄ መሆኑ ይነገርለታል።

የጉበት ስራን ያፋጥናል ፡- የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ በቫይታሚኖች፣ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትስ የበለፀገ ሲሆን ፥ የጉበትን ጤና ይጠብቃል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ በተፈጥሮ አልካላይን በመሆኑ በሰውነት ውስጥ ያለውን የኤሌክትሮላይት ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

ካንሰርን ለመዋጋት፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ውስጥ የሚገኘው ፖሊፊኖል የተባለ ተክል ከፍተኛ ፀረ-ባክቴሪያ እና ፀረ-ካንሰር ነው።

ከዚህ አንጻርም የሸንኮራ አገዳ ጭማቂን በምግብዎ በመደበኛነት እንዲጠቀሙ ይመክራል፡፡

የምግብ መፈጨትን ያግዛል፡- በሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ውስጥ ያለው ፖታሺየም በሆድ ውስጥ ያለውን የአሲድና የውሃ መጠን ያስተካክላል፡፡

የሸንኮራ አገዳ ጁስ መጠጣት አንድ ሰው ውሀ እንዲጠጣ ስለሚያደርግ ድርቀትን ይከላከላል፤ በተጨማሪም የሆድ በሽታን ለመከላከል ይረዳል፡፡

የኩላሊት ጤናን ይጠብቃል፦ ዜሮ ኮሌስትሮል ፣ ዝቅተኛ-ሶዲየም እና ምንም ስብ የሌለው በመሆኑ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለኩላሊት ጤናማነት ፍቱን ነው ይባልለታል።

የሸንኮራ አገዳ በሎሚ ጁስ እና በኮኮናት ውሃ ከተጠጣ የሰውነት መቆጣትን ለመቀነስ እንዲሁም እንደ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን፣ የኩላሊት ጠጠር እና ፕሮስታታይተስ ያሉ ምልክቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ይረዳል።

በድሮ ጊዜ የሸንኮራ አገዳ ማኘክ ለታዳጊ ህፃናት እና ጎረምሶች መደበኛ ጊዜ ማሳለፊያ ነበር።

በካልሲየም የበለጸገው የሸንኮራ አገዳ የአጥንትና ጥርስ ጥንካሬ እንዲኖረው እና ጤንነትን በመጠበቅም ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

እንደ ብጉር ያሉ የቆዳ ችግሮችን ለማከም እንደሚረዳ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩ ከኽልዚፋይሚ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.