Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ባጫ በኬንያ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በሀገሪቱ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የኬንያ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ተነሳሽነት የተጀመረ ሲሆን በኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ አስተዳደር ካቢኔ ፀድቆ በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

የኬንያን የመሬት ገጽታ እና ስነ-ምህዳር መልሶ ያቋቁማል የተባለው ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሀገሪቱ በመጪዎቹ አስርት አመታት 15 ቢሊየኝ ችግኞችን ለመትከል ያቀደችው ፕሮግራም አንድ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ኤምባሲው ባለፈው አመት የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል በሆነው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በናይሮቢ ከ1 ሺህ በላይ ችግኞችን መትክሉ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ አምስት አመታትም ኤምባሲው በኬንያ ከ32 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.