Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ቢሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ነው፡፡

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም፡-

• በአማራ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

• አለመግባባቶች ወደ ግጭት ከመግባታቸው በፊት የመንግሥት ዝግጁነት እንዴት ይገለጻል?

• የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመመከት ረገድ ምን እየተሠራ ነው?

• የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና አዳዲስ በመጀመር የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ በመንግሥት በኩል ምን እየተሠራ ነው?

• እንደ ሀገር ካለው የባሕር ወደብ ፍላጎት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ብዥታዎች ስላሉ ግልጽ ለማድረግ ያህል ማብራሪያ ቢሰጥ፣

• በአጠቃላይ ፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር በተለይም አንዳንድ ለብልሹ አሠራር የሚያጋለጡ ዘርፎችን ከሌብነት በጸዳ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደመንግሥት ያለው ቁርጠኝነት ቢገለጽ፣

• ለሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ስኬት የመንግሥት ድጋፍ ቢጠቀስ፣

• የዜጎች ከቦታ ቦታ በነጻነት መንቀሳቀስና መሥራት አደጋ ላይ እየወደቀ ነው፤ መንግሥት ምን መፍትሔ ዘይዷል? ከንጥል ትርክት በመውጣት የጋራ ትርክት እንዲኖርስ ምን ታስቧል?

• የሕግ የበላይነት በአንዳንድ አካባቢዎች ጥያቄ ውስጥ ወድቋል፤ በመንግሥት በኩል እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች በዝርዝር ቢብራሩ፤

• የመሠረተ-ልማት ፍትሐዊ ክፍፍል የለም፤ ከዚህ አንጻር የመንግሥት አቋም ምንድን ነው?’

• ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ መንግሥት ያስቀመጠው የተለየ አቅጣጫ ካለ ቢገለጽ፤

• በብልሹ አሠራሮች ውስጥ ሆነው ሕዝብን እያማረሩ በሚገኙ አመራሮች ላይ መንግሥት ርምጃ ለመውሰድ ያለው ዝግጁነት ቢብራራ፤

• የፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጻም በምን ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው የሚሉና ሌሎች ማብራሪያና ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎች የምክር ቤቱ አባላት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

በዮሐንስ ደርበው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.