የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስትሯ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

May 22, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን የጾም ወቅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያሳየውን ጥንቃቄ በበዓሉ ወቅትም መድገም እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።