Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሥራ እድል ፈጠራን፣ ሌብነትን፣ የጫካ ፕሮጀክትንና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ ከሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉ባለፉት ወራት እስካሁን ባለው ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰው ስራ ይዟል፣ በውጭ ሀገር ብቻ 100 ሺህ ሰው በህጋዊ መንገድ የሥራ ስምሪት ተሰርቷል፣

👉ወጣቶች በቀንና በማታ ስራ የሚያገኙባቸው ፕሮጀክቶች ተፈጥረዋል፤ መስፋት አለባቸው፣

👉ብዙ ህዝብ ስላለን ብዙ ስራ ካልፈጠርን በስተቀር የስራ አጥነት ጉዳይ ውዝፍ የሚቀጥል እዳ ስለሆነ በስፋት መረባረብ ያስፈልጋል፣

👉የጫካ ፕሮጀክት እስከ 100 ኪሎ ሎሜትር ሜትር መንገድ የሚሰራበት ፕሮጀክት ነው፣

👉የጫካ ፕሮጀክት አሁን ያለችውን አዲስ አበባ ግማሽ የሚያክል ከተማ የሚገነባ ፕሮጀክት ነው፣

👉አርተፊሻል ኢንተለጀንስ የዓለምን ሁኔታ ይወስናል፣

👉ትውልድ ላይ አበክረን የምንሰራው፣ የምናስተምርው ጥፋቱንም ልማቱንም አስተካክለው መጠቀም እንዲችሉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም ቴክኖሎጂውን ማወቅ እና መጠቀም ይገባል፣

👉በተለያዩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት አዳዲስ ፈጠራ ያላቸው ወጣቶች እየወጡ ነው፤ በቅርቡ የነበረው ውድድርም ይህንን ያመላከተ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.